ስለ የህጻናት መዋያ እቃ/ ኪንደር ኪት
ለልጆች፣ መጫወትና መማር እጅ ለእጅ ተያይዘው የሚሄዱ ናቸው። ጨዋታ፤ ልጆች ስለ ራሳቸው የሚያውቁበት እና በዙርያቸው ስላለው ዓለም የሚማሩበት መንገድ ነው። ወላጆችና ቤተሰቦች በዛ ጉዞ ውስጥ ትልቅ ድርሻ አላቸው። በልጃችሁ የጻን መዋያ እቃ/ኪንድር ኪት ውስጥ ያለው ነገር ሁሉ በቤተሰብ መልክ እንዲካፈልና እንዲደሰት ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
በህፃናት ማሳደጊያ ውስጥ የቪክቶሪያን የመጀመሪያ ዓመታት ትምህርት እና ልማት መርሃ ግብር (VEYLDF) በአምስት የመማር እና የእድገት ውጤቶች ላይ ልጃችሁ እንዲያድግ እና እንዲቆይ የሚደግፉ የመማር ተሞክሮዎችን ለመፍጠር ያገለግል ነበር። እነዚህ አምስት ውጤቶች የሚከተሉት ናቸው፦
- መለያ
- ማህበረሰብ
- ደህንነት
- መማር
- የሐሳብ ልውውጥ ማድረግ
የተረት ኪዩቦች
ልጆች የዕለት ተዕለት ተሞክሯቸውን በማስተዋል ረገድ ተረት መናገር በጣም አስፈላጊ ነው። ማንበብና መጻፍ እንዲችሉ የሚረዳ ከመሆኑም በላይ በዙሪያቸው ያሉ ሰዎችን እንዴት የሀሳብ ልውውጥ ማድረግ እንደሚቻል እንዲገነዘቡ ይረዳቸዋል።
ልጃችሁ በእንግሊዝኛ ውስጥ ባሉ ኪዩቦች ወይም በሌሎች ቋንቋዎች አዳዲስ ቃላትን እንዲማር መርዳት ትችላላችሁ።
- ተራዎን ጠብቀው የስዕሎቹን ስም ይጥሩ
- ከእነሱ ጋር መገንባት
- ታሪኮች ይንገሯቸው
- ጥያቄዎች ይጠይቁ
ስእል መሳያ ክሬይኖች/Crayons እና የስነ-ጥበብ ፓድ
በክሬይኖች መሳል ለመማር ብዙ መንገዶችን ይሰጣል፦
- እንደ እርሳስ መያዝ ያሉ ጥሩ የአእምሮ ቅንጂት ችሎታዎችን ማሻሻል
- የእጅ-ለአይን ቅንጅት
- ስለ ቀለም እና ቅርጽ መማር
- የፈጠራ ችሎታን በወረቀት እና በሌሎች ቁሳቁሶች መግለጽ።
ከሁሉ በላይ ደግሞ ልጃችሁ ሀሳቡን በልበ ሙሉነትና በበሙሉ እምነት መግለጽን ይማራል። አንዳንድ ልጆች በአንተ ዘንድ የማይታወቁ ምልክቶችን እያደረጉ ይሆናል፤ ይህ ደግሞ ምንም ችግር የለውም። ይህ ስዕል ለመሳል መማር ይህ የተለመደ አሰራር ሂደት ነው።
- ሀሳቦችን ለማዳበር ስነ-ጥበብ/አርት ፓድ መጠቀም
- የቤተሰብ ስዕል ተሞክሮዎችን እንዲስሉ ማበረታታት
- ስዕል ስትስሉ ተነጋገሩ
- የቀለሞችን እና የቅርጾችን ስም ይጥሩ
ዘሮች
ዘሮችን ከልጆች ጋር መትከል የተፈጥሮን አስደናቂነት ለማየት የሚያስችል በሳይንስ ላይ የተመሰረተ የትምህርት ተሞክሮ ነው። ስለ ተፈጥሮ ይማራሉ፣ ቋንቋ ይሰራሉ እንዲሁም ቀለል ያሉ መመሪያዎችን መከተልን ይማራሉ። በተጨማሪም ነገሮችን በጊዜ ሂደት እንዴት መመልከት እንደሚችሉ ይማራሉ።
- ስለ ተክሎች ተነጋገሩ እንዲሁም ክፍሎቻቸውን ስም ይጥሩ
- በጋራ ሆነው ይትከሏቸው
- በየጠዋቱ እድገቱን ይከታተሉ
- በገበያ ላይ ያሉ ፍራፍሬ እና አትክልቶችን ስም ይጥሩ
እንስሳቶችን በክር መስራት
የቅድሚያ ልጅነት ጊዜ ልጆች በእጃቸው፣ በጣቶቹ፣ በክንዳቸው፣ በእግራቸውና በጣቶቻቸው ያሉትን ትናንሽ ጡንቻዎች ይበልጥ መቆጣጠር የሚጀምሩት ገና በልጅነታቸው ነው። በእጆችና በጣቶች ውስጥ ጥሩ የቁጥጥር ጡንቻዎችን ማዳበር ለልጆች ራስን ለመንከባከብና በኋላ ላይ ለመጻፍ አስፈላጊ ነው። ልጃችሁ በመጫወቻ፣ በክራዮን መሳያ ወይም በክር የተሰራ እንስሳት በመጠቀም ጥሩ የግንዛቤ ሞተር ችሎታ ማዳበር ይችላል። ጥሩ የግንዛቤ ሞተር ችሎታ መለማመድ የምትችልባቸው አንዳንድ መንገዶች ከዚህ በታች ቀርበዋል፦
- በእንስሳው ቀዳዳ በኩል መፍተል
- ኪንደር ኪትን መክፈት እና መዝጋት
- ዚፖችን ወይም ቁልፎችን መቆለፍን ይለማመዱ
- በእጆች እና በጣቶች የልጥ ጭቃዎችን መደምጠጥ
የመጨወቻ ጭቃ/Playdough
ልጅዎ የመጫወቻ ጭቃ/playdough በመፍጠር ላይ እያሉ የተለያዩ በጣም አስፈላ ነገሮችን እንደሚሰሩ ነው።
- ጥሩ የማስተዋል ሞተር ችሎታዎችን እያሻሻሉ ነው
- የስሜት ሕዋሶቻቸውን በመጠቀም ምርምር እያደረጉ ሲሆን
- ያላቸውን ዓይነ ሕሊና የማየት ችሎታ እየተጠቀሙ ነው።
ለልጃችሁ በጨዋታ ጭቃ/playdough ፈጠራን መፍጠር ለልጃችሁ ትምህርት ላይ ጠቃሚ ክፍል ነው።
- ኳስ ማንከባለል፤ ማንጠልጠል፤ መጨፍለቅ፤ መጨፍለቅ
- ስለዚህ ጉዳይ ተነጋገሩ
- ሌሎች ነገሮችን መጨምር እንደ እንጨቶች ወይም ላባዎች ወይም ዛጎሎችን የመሰሉ
- በምታገኙት ነገር ላይ ንድፍ ይኑራችሁ
የልጆች መጽሐፍት
መጽሐፎችን አብረን ማንበብ በቤተሰብ አንድ ላይ ለመቀራረብና ጊዜ ለማሳለፍ የሚያስችል ግሩም መንገድ ነው። የማንበብ እና መጻፍ ክህሎትን ለማሳደግ ከሚረዱ በጣም አስፈላጊ መንገዶች አንዱ ነው። ከልጃችሁ ጋር ቋሚ የሆነ ታሪክ ማጋራት በዓይነ ሕሊናቸው የማየት ችሎታቸውንና የቃላት አጠቃቀማቸውን ያሻሽላል።
- አንድ ላይ መጽሐፍ ይምረጡ
- ለመቀመጥ እና ለማንበብ ደስ የሚል ቦታ መፈለግ
- ገጾቹን እንዲገለብጡ ማድረግ
- የተለያዩ ድምፆችን ለገጸ-ባህሪያት ይጠቀሙ፤ ስለ ስዕሎቹ ይነጋገሩ
ሙዚቃ ፈጣሪዎች
ሙዚቃ ለልጆች ትምህርትና እድገት ብዙ ጥቅሞች አሉት። ሙዚቃ መፍጠር ልጃችሁ አዳዲስ ቃላትን እንዲማር፣ ከቤተሰብ ጋር አብሮ መዝሙሮችን እንዲዘምርና ስለ ራሳቸው ጥሩ ስሜት እንዲሰማው የሚያስችል አስደሳች መንገድ ነው። መደነስ፣ መዘመር፣ መንቀሳቀስ፣ ማዘለል እና ካስታኔትን መንካት ሁሉም የአስደሳች ነገር አካል ናቸው።
ከልጅህ ጋር በሙዚቃ ለመደሰት የተወሰኑ ሃሳቦች እነዚህ ናቸው፦
- ለምትወዱት ሙዚቃ መጨፈር እና መወዛወዝ
- ቁጥሮችን ለማስተማር የሙዚቃ ቢቶችን መቁጠር
- አጭር የዜማ ዘፈኖች ይለማመዱ
- ክፍለ-ቃላቶችን ለመቁጠር ካስታኔት ይጠቀሙ
ኪት እንቅስቃሴ መያዣ/ Kit Activity Case
የኪት እንቅስቃሴ መያዣ መጽሐፍት እና አሻንጉሊቶችን ለመሸከም ብቻ አይደለም - በብዙ መንገዶች ትምህርት እና እድገት ለመደገፍ ሊያገለግል ይችላል። ነጭ ሰለዳ/Whiteboard ገጽ በማግኔት ለማጫወት, playdough (ዱቡልብል የመጫወቻ ጭቃ) እና ስዕል ለመሳል በጣም ጥሩ ናቸው። ኪትን ወደ የመሳያ ማስደገፍያ ይጠፉ። አረንጓዴው ገጽ በዓይነ ህሊና ሁኔታ ለመጫወት እንዲውል ኪትን ለጥ ባለ ቦታ በመዘርጋት ያስቀምጡ። የውቅያኖስ ትዕይንት ወይም የከተማ ጎዳና ሊሆን ይችላል። ወደ መዋለ ሕጻናት የምትጓዝበትን መንገድ እንደገና ይፍጠሩ። የእቃ ኪትን መያዣን ለመጠቀም የሚረዱ ሌሎች የተወሰኑ መንገዶች ከዚህ በታች ቀርበዋል፦
- አዲስ ዓለም መፍጠር
- Playdough playmat
- ለመጽሃፍት እና ለአሻንጉሊቶች የሚሆን ቦርሳ ይያዙ
- እንደ አስመሳይ አጨዋወት
የእቃ/ኪት እንቅስቃሴ መያዣ ለአካባቢ ተስማሚ ውጤት እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ይህ መሳሪያ በተቻለ መጠን እንደገና ጥቅም ላይ ከዋሉ ነገሮች የተሠራ ሲሆን የልጃችሁን የመዋዕለ ሕፃናት ማሰሮዎች ለማስቀመጥ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
ማህበረሰብን መገንባት
ቪክቶሪያ የተለያየ ማህበረሰብ ያላት እንደሆነች፤ የብዙ ባህሎችና የተለያዩ ቋንቋዎች መኖሪያ ናት። አሁን የሆነውን ማንነት ከሚያደርጉን ነገሮች መካከል የተለያየ ልዩነት ትልቅ ድርሻ አለው። በኪት ውስጥ የሚገኙት እቃዎች ስለተለያዩ ማህበረሰቦች የሚደረገውን ውይይት ለመረዳት ይረዳሉ።
- ለልጆች፣ መጫወትና መማር እጅ ለእጅ ተያይዘው የሚሄዱ ናቸው። ጭዋታ፤ ልጆች ስለ ራሳቸው የሚያውቁበት እና የሚማሩበት መንገድ ነው።
- ከሌሎች ባህሎች ወይም ከራስዎ ምግብ ለመስራት ለመምሰል መጫውቻውን/playdough ይጠቀሙ
- ከሌሎች ባህሎች ወይም ከራስዎ ባህሎች ባህላዊ ሙዚቃ እያዳመጥክ ምልክቶችን/ካስታኔቶችን ይጫኑ
- ስለ ሌሎች ሃገሮች እና ስለ የሃገራቸው እንስሳት ከልጅዎ ጋር ይነጋገሩ
መጽሐፍት በኣውስላን/Auslan ቋንቋ
በ 2023 Kinder Kit ውስጥ የተካተቱት ሁሉም መጽሃፎች ኦውስላን/Auslan ትርጉሞች አሏቸው። ኦውስላንና የጽሁፍ መግለጫ በቪዲዮዎቹም ውስጥ ተካትተዋል።
አውስላን አብዛኛው የአውስትራሊያ መስማት የተሳናቸው ማህበረሰብ የሚጠቀምበት የምልክት ቋንቋ ሲሆን በቪክቶሪያ የመጀመሪያ ልጅነት ቋንቋዎች ፕሮግራም ክፍል አካል ሲሆን ይህም በአንዳንድ የአራት ዓመት እድሜ መውእለ ህጻናት ይቀርባል።
ልጆች ገና በለጋ እድሜያቸው በሌላ ቋንቋ መማር ብዙ ጥቅም እንዳለው የትምህርት ባለሙያዎች ደርሰውበታል፣ የሚከተሉት ጨምሮ፦
- የቅድመ-ንባብ እና ቅድመ-ጽሑፍ ችሎታን መጨመር
- የማገናዘብ ማሰብ ችሎታ እንደ ሁኔታው መለዋወጥ
- ለራስ ጥሩ ግምትንና ደህንነትን ማጠናከር
- የተጠናቀረ የባህል መለያ።
ማንነትን ማክበር
የመጀመሪያ የሃገር ህዝባችን ባህሎች በአውስትራሊያ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ክፍል ነው። ህጻናት በሙሉ ስለ ሁሉም ባህሎች እንዲማሩ ማበረታታት ማስተዋልን፣ ተቀባይነትንና ኩራትን ይገነባል። የመጀመሪያ የሃገር ደራሲዎቻችንና ለኪትስ መስራቾች በዓል ለማክበር ኩራት ይሰማናል። የታሪክ ብሎኮች፣ ለምሳሌ ያህል፣ እነዚህ ተረቶች የአቦርጂኖች ባህላዊ ልምድን የሚያበረታቱ አፈ ታሪክን የሚያሳዩ ናቸው። ልጃችሁ ስለ የመጀመሪያ ሃገር ህዝቦች ልምድና ባህል ይበልጥ እንዲማር የሚረዱት እንቅስቃሴዎች የሚከተሉት ናቸው፦
- ለእንስሳት ወይም እቃዎች የአቦርጅኖች ምልክቶችን መማር
- ስለ አቦርጂናሎች መሪዎች ወይም ስለ ስፖርት ጀግኖች መነጋገር
- ስለ የመጀመርያ ብሔር ባህሎችና ሕዝቦች በበለጠ መማር
ደህንነት እና ተጨማሪ ድጋፍ
ሁሉም ልጆች የሚማሩት በተለያየ መንገድና በራሳቸው ፍጥነት ነው። ኪንድር ኪት ለልጃችሁ የተለያዩ ችሎታዎችን ለመፈታተን በተለያዩ መንገዶች ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ መጻሕፍትንና አሻንጉሊቶችን ያቀርባል። ይሁን እንጂ አንዳንድ ጊዜ ለልጃችሁ ትምህርት ተጨማሪ ድጋፍ ያስፈልጋችኋል። አንተም ሆንክ ልጅህ ተጨማሪ ድጋፍ ሊያስፈልግህ እንደሚችል ካሰብክ ይህን ማድረግ የምትችልባቸው በርካታ መንገዶች አሉ፦
- የቪክቶሪያ የህጻናት ማሳደጊያ መምህራን የመርዳት ችሎታና እውቀት አላቸው። ስለ ጥያቄዎችዎ ከልጅዎ አስተማሪ ጋር ይነጋገሩ
- ባልዎት ጥያቄዎች ላይ ለመወያየት ሀኪምዎን ወይም የእናትና ህጻን ጤና ጥበቃ ነርስን ለማየት ቀጠሮ ይያዙ
- በነጻ ምስጥራዊ የሆነ መማክርት እና ድጋፍ ለማግኘት ለወላጅ መስመር/Parentline በስልክ 13 2289 ይደውሉ
የመዋእለ ሕጻናት (ኪንደር) መሳሪያዎች (ኪት) ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ሁሉን የሚያካትቱ ናቸው
በኪንደር እቃ መያዣ ውስጥ የሚገኙት ሁሉም እቃዎች ከደህንነት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሲሆን ኪንደር ላይ ለሚሳተፉ ለሶስት ዓመት ልጆችም ተስማሚ ናቸው።
ጥቂት ቁጥር ያላቸው እቃዎች ትናንሽ ክፍሎች ስላላቸው ከሶስት ዓመት እድሜ በታች የሆኑ ህጻናት ሊጠቀሙባቸው አይገባም።
እነዚህ የነጭ ሰሌዳ መጻፊያዎችና በመካከሉ የተገጠመ ትንሽ ማግኔት ያለው ማግኔቲክ ማጥፊያናቸው።
እነዚህ እቃዎች በውጨኛው ማሸጊያ ላይ ተገዚ የሆነ ማስጠንቀቂያ የተለጠፈባቸው ከመሆናቸውም ባሻገር ጥቅም ላይ መዋል ያለባቸው ለታቀዱበት ዓላማ ብቻ ነው።
ከሶስት ዓመት እድሜ በታች የሆነ ልጅ ካለዎት፣ እባክዎን እነዚህን እቃዎች ማግኘት በማይችሉበት ቦታ ላይ ያስቀምጧቸው።
በሁሉም የእድሜ ክልል ለሚገኙ ልጆች ለሚሆኑ መጫወቻዎች ሁሉ፣ ወላጆችም ሆኑ አሳዳጊዎች ጥቅም ላይ እንዲውሉ ከማድረጋቸው በፊት ሁልጊዜ መፈተሽ እና የተበላሸወይም የተቀደደ ነገር በሚኖር ጊዜ ማስወገድ አለባቸው።
Reviewed 21 September 2023