JavaScript is required

መዋዕለ ህጻናት (ኪንደር) እንዴት እንደሚሠራ (How kinder works) - አማርኛ (Amharic)

መዋዕለ ህጻናት (ኪንደር)፣ እንዲሁም 'ኪንደርጋርተን' ወይም 'የመጀመሪያው የልጅነት ትምህርት' በመባል የሚታወቅ ሲሆን፣ የልጅዎ እድገት እና ትምህርት አስፈላጊ አካል ነው። ልጅዎን ለሁለት ዓመት በመዋዕለ ህጻናት ፕሮግራም ማስመዝገብ ችሎታውን እንዲያዳብር እና በህይወት እና በትምህርት ቤት ጥሩ ውጤት እንዲያገኙ ይረዳል።

የመዋዕለ ህፃናት ሰዓታት፦

የሶስት አመት ልጅ መዋዕለ ህፃናት ፕሮግራሞች በየሳምንቱ ከ 5 እስከ 15 ሰአታት እና የአራት አመት ህፃናት ፕሮግራሞች ለ 15 ሰአታት የሚሰጡ ናቸው።

የተረጋገጡ ውጤቶች:-

ወደ መዋዕለ ህፃናት (ኪንደር) ፕሮግራም የሚሄዱ ልጆች እንደ ቁጥሮች መቁጠር፣ ቁጥሮች እና ፊደሎች መለየት እና ችግሮችን መፍታት እንዴት እንደሚችሉ የመሳሰሉ ክህሎቶችን ማዳበር ይጀምራሉ። በመዋዕለ ህፃናት (ኪንደር) ልጆችዎ በራስ መተማመን እና ነፃነት ይገነባሉ ብሎም ማህበራዊ እና ስሜታዊ ክህሎቶችን ይማራሉ። እነሱ ይገናኛሉ እና አዲስ ጓደኞች ያፈራሉ።

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ትምህርት ከመጀመራቸው በፊት ሁለት ወይም 3 ዓመት የመዋዕለ ህጻናት መርሐ ግብር የተከታተሉ ተማሪዎች፣ በ16 ዓመታቸው በእንግሊዝኛ እና በሒሳብ ከሌላው የበለጠ ውጤት ነበራቸው።

ወላጆች እና የመዋዕለ ህፃናት (ኪንደር) አስተማሪዎች እንዴት አብረው እንደሚሠሩ:-

መዋዕለ ህፃናት (ኪንደር) በወላጆች/አሳዳጊዎች፣ ቤተሰቦች እና አስተማሪዎች መካከል እንደ አጋርነት ሲካሄድ በተሻለ ሁኔታ ይሰራል። እንደ ወላጅ/ተንከባካቢ፣ እርስዎ የልጅዎ እድገት በጣም አስፈላጊ አካል ነዎት። እርስዎ ትክክል የሆነውን ከስህተት፣ ቋንቋዎን፣ ባህልዎን እና እንደ ደግነትና መከባበር ያሉ እሴቶችን ያስተምሯቸዋል። መምህራን በመዋዕለ ህፃናት (ኪንደር) ላይ ስለሚሆነው ነገር እና ልጅዎ በቤት ውስጥ መማር እንዲቀጥል ስለሚረዱ መንገዶች ይነግሩዎታል። ስለልጅዎ ፍላጎቶች እና እንዴት መማር እንደሚፈልግ ማወቅ ይፈልጋሉ።

በማንኛውም ጊዜ አስተርጓሚ እንዲያዘጋጅ የመዋዕለ ህፃናት (ኪንደር) አስተማሪዎን መጠየቅ ይችላሉ። ይህ በጣቢያው ላይ ወይም በስልክ ወይም በቪዲዮ ሊሆን ይችላል። ይህንን አገልግሎት ለማግኘት ቤተሰቦች ምንም ወጪ አያወጡም።

በመዋዕለ ህፃናት ውስጥ ምን ይከሰታል፦

አስተማሪዎች ልጆች በመጫወት እንዲማሩ ያበረታታሉ። የሚደረጉ ተግባራት፣ መሳል፣ መዘመር፣ ተራራ መውጣት፣ መቆፈር እና ከቤት ውጪ መሮጥ፣ በአሻንጉሊት መጫወት እና መጽሃፍ ማንበብን ሊያካትቱ ይችላሉ። ጨዋታ ልጆች ከሌሎች ጋር በመተባበር ነገሮች ሲጋሩ እና ተራ በተራ ሲጫወቱ፣ ሃሳባቸውን እንዲጠቀሙ እና ግኝቶችን እንዲያገኙ ያበረታታል። ልጆች እንግሊዝኛን እንዴት እንደሚናገሩ እና እንደሚረዱ ጨምሮ ስለ ድምጾች፣ ቃላት እና ቋንቋ ይማራሉ።

መዋዕለ ህፃናት (ኪንደር) የመድብለ ባህላዊ ማህበረሰባችን አካል ነው:-

የመዋዕለ ህፃናት (ኪንደር) ፕሮግራሞች ከሁሉም አስተዳደግ (ዳራ) የመጡ ወላጆችን የማህበረሰባቸው አካል እንዲሆኑ በደስታ ይቀበላሉ። ወላጆች የሚገናኙበት እና ታሪኮችን የሚለዋወጡበት እና እርስበርስ የሚማሩበት ቦታ ናቸው።

አስተማሪዎች ስለልጅዎ እና ስለ ባህልዎ ማወቅ ይፈልጋሉ። ይህ ለልጅዎ ትርጉም ያላቸውን ፕሮግራሞች እንዲያዘጋጁ ይረዳቸዋል፣ ይህም በባህላዊ ቀናት እና ዝግጅቶች ላይ የተመሰረቱ እንቅስቃሴዎችን እና በቪክቶሪያ ውስጥ ያለውን ልዩነት ማክበርን ያካትታል።

አስተማሪዎች ሁሉንም ልጆች በእንቅስቃሴዎች ውስጥ ያሳትፋሉ፣ ስለዚህ እንግሊዝኛ የማይናገሩ ልጆች እንደሌሎች የመጫወት እና የመማር እድሎች አሏቸው። አንዳንድ የመዋዕለ ሕፃናት ፕሮግራሞች ትንሽ እንግሊዝኛ የሚናገሩ ወይም ጭራሽ የማይናገሩ ልጆችን የሚረዱ ሁለት ቋንቋ ተናጋሪ አስተማሪዎች አሏቸው። እንዲሁም ልጆች ከሌሎች ጋር እንዲስማሙ እና ሌሎችን እንዲቀበሉ እና የባህል ልዩነቶችን እንዲያከብሩ ይማራሉ።

የመዋለ ሕጻናት ፕሮግራሞች ዓይነቶች

ልጆች የሶስት አመት ልጅ መዋዕለ ህጻናትን መርሀ ግብር በረዥም (ሙሉ) ቀን ማቆያ (የህጻን እንክብካቤ ተብሎም ይጠራል) ማእከል ወይም ብቻውን የሚሰራ (የክፍለ ጊዜ ኣገልግሎት ተብሎም በሚጠራው) መዋዕለ ህፃናት መከታተል ይችላሉ። እነዚህ አገልግሎቶች ብዙውን ጊዜ የአራት ዓመት ልጅ መዋዕለ ህፃናት ፕሮግራም ይሰጣሉ።

የረጅም (ሙሉ) ቀን የእንክብካቤ ማዕከል የሙሉ ቀን ትምህርት እና እንክብካቤ መስጠት ይችላል፣ ይህም የመዋዕለ ህፃናት (ኪንደር) ፕሮግራምን ይጨምራል። በአስተማሪ የሚመራው የመዋዕለ ህፃናት (ኪንደር) ፕሮግራም ከተጨማሪ የትምሕርት እና እንክብካቤ ሰዓታት ጋር ሊጣመር ይችላል።

ለብቻው በሚሰራ አገልግሎት፣ የመዋዕለ ህጻናት (ኪንደር) ፕሮግራም የሚሰራው በተወሰኑ ቀናት እና በተወሰኑ ጊዜያት ብቻ ነው።  ለብቻው የሚሰራ አገልግሎት በዓመት በትምህርት ጊዜ ለ40 ሳምንታት የሚሠራው ሲሆን ከትምህርት ቤቶች ጋር በተመሳሳይ ጊዜ እረፍት ያደርጋል። እነዚህ ቀናት እና ሰዓቶች የሚወሰኑት በመዋዕለ ህጻናት (ኪንደር) አገልግሎቱ ነው።

Updated