Victoria government logo

Three-Year-Old Kindergarten brochure - Amharic

የቪክቶሪያ መንግሥት በአስር ዓመታት ውስጥ ሁለገብ የገንዘብ ድጋፍ የተደረገለት የሦስት ዓመት ልጆች መዋለ-ህፃናት ለማስተዋወቅ ወደ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ሥራ ላይ እያዋለ ነው - እናም ይህ አሁን በመላው የክልሉ ግዛት ይገኛል፡፡

የቪክቶሪያ መንግሥት በአስር ዓመታት ውስጥ ሁለገብ የገንዘብ ድጋፍ የተደረገለት የሦስት ዓመት ልጆች መዋለ-ህፃናት ለማስተዋወቅ ወደ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ሥራ ላይ እያዋለ ነው - እናም ይህ አሁን በመላው የክልሉ ግዛት ይገኛል፡፡

ይህ ማለት ለቪክቶሪያ ልጆች ሌላ የመማር፣

የማደግ፣ የመጫወት እና ጓደኛ የማፍራት ዓመት ማለት ነው፡፡

ከሶስት አመት ጀምሮ ጥራት ባለው የመዋዕለ ህፃናት መርሃግብር ውስጥ መሳተፍ የልጆችን የመማር፣ የዕድገት፣ የጤና እና የደህንነት ውጤቶችን ከፍ ያደርጋል፡፡

ትናንሽ ልጆች በዙሪያቸው ስላለው ዓለም በጨዋታ መልክ ይማራሉ

በጨዋታ ላይ የተመሠረተ ትምህርት ትናንሽ ልጆች በተሻለ ሁኔታ የሚማሩበት መንገድ ነው። ልጆች አይነህሊናቸውን እንዲጠቀሙ፣ የቋንቋ ችሎታቸውን እንዲገነቡ እና ስለ ቁጥሮች እና ቅጦች እንዲማሩ እድል ይሰጣቸዋል፡፡ እንዲሁም ከሌሎች ጋር እንዴት ተስማምተው መኖር፣ መጋራት፣ ማዳመጥ እና ስሜታቸውን መምራት ወይም መቆጣጠር እንደሚችሉ ይማራሉ፡፡

በቪክቶሪያ ውስጥ ያሉ ሁሉም ልጆች ለሁለት ዓመት የገንዘብ ወጪው የተሸፈነ የመዋለ-ህፃናት ቆይታን ያገኛሉ

በመላው የክልሉ ግዛት ያሉ ሕፃናት ከ 2022 ጀምሮ ቢያንስ በየሳምንቱ የአምስት ሰዓት የገንዘብ ወጪው የተሸፈነለት የመዋዕለ-ህፃናት መርሃግብር ተጠቃሚ ይሆናሉ። እስከ 2029 ባለው ጊዜ ውስጥ ሰዓቶቹ በሳምንት ወደ 15 ሰዓታት ይጨምራሉ።

ልጅዎ የሚሄድበት መዋዕለ ህፃናት የትኛውም ይሁን፣ መምህራን እና የሰለጠኑ አስተማሪዎች መርሃግብሩን ይመራሉ

የመዋለ-ህፃናት መርሃግብርን ልጆች የረጅም ወይም የሙሉ ቀን እንክብካቤ (የህጻን እንክብካቤ) በሚሰጡ አገልግሎቶችም ይሁን በተናጥል ባለ መዋዕለ-ህፃናት ውስጥ ሆነው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

ትናንሽ ልጆች ስለ ዓለም በጨዋታ አማካይነት ይማራሉ

እንዴት ከሌሎች ጋር ተስማምተው እንደሚኖሩ፣ እንደሚጋሩ፣ እንደሚያዳምጡ፣ እና ስሜታቸውን መምራት ወይም መቆጣጠር እንደሚችሉ ይማራሉ

በመዋዕለ-ህፃናት መርሃግብር ውስጥ፣ ልጆች የቋንቋ ችሎታቸውን ለመገንባት እና ስለ ቁጥሮች እና ቅጦች ለመማር ጨዋታን ይጠቀማሉ

መምህራን እና አስተማሪዎች ልጆች ጉጉ፣ የፈጠራ ችሎታ ያላቸው እና ስለ ትምህርት ልበ ሙሉ እንዲሆኑ ይረዳሉ

    • ራሳቸውን በቻሉ መዋዕለ-ህፃናት
      • የመዋዕለ-ህጻናት መርሃግብሮች - ልጆች ለተወሰኑ ቀናት እና ሰዓታት የመዋዕለ-ህፃናት መርሃግብርን ይከታተላሉ
    • የረጅም ወይም የሙሉ ቀን እንክብካቤ አገልግሎቶች
      • የመዋዕለ-ህጻናት መርሃግብሮች - ልጆች በረጅም ወይም በሙሉ ቀን እንክብካቤ የሚያሳልፉት ጊዜ ውስጥ የመዋዕለ-ህፃናት መርሃግብርን እንደ አንድ አካል አድርገው ይሳተፋሉ
      • ትምህርት እና እንክብካቤ - የረጅም ወይም የሙሉ ቀን እንክብካቤ አገልግሎቶች የቅድመ መደበኛ ትምህርት እና እድሜያቸው በ 0 እና 6 ዓመታት መካከል ላሉ ሕፃናት እንክብካቤ ይሰጣሉ

    ሁሉም የገንዘብ ወጪ የሚሸፈንላቸው የመዋዕለ-ህፃናት መርሃግብሮች የመንግስትን የደህንነት እና የጥራት መመሪያዎች ማሟላት ያለባቸው እና ከቪክቶሪያ የመጀመሪያዎቹ ዓመታት የመማር እና የዕድገት ማዕቀፍ ጋር በሚጣጣም መልኩ የተቀረፁ ናቸው።

    አንድ የረጅም ወይም የሙሉ ቀን እንክብካቤ ማዕከል የመዋዕለ-ህፃናት መርሃግብርን ጨምሮ የሙሉ ቀን ትምህርት እና እንክብካቤ ሊያቀርብ ይችላል፡፡ በአስተማሪ የሚመራው የመዋዕለ-ህፃናት መርሃግብር ከተጨማሪ ሰዓታት ትምህርት እና እንክብካቤ ጋር የተሰባጠረ ነው። በተናጥል አገልግሎት ውስጥ፣ የመዋዕለ-ህፃናት መርሃግብር በተወሰኑ ቀናት እና በተወሰኑ ጊዜያት ብቻ ይካሄዳል፡፡ እነዚህ ቀናት እና ሰዓቶች በመዋዕለ-ህፃናት አገልግሎቱ የተወሰኑ ናቸው።

    ልጅዎን ወዴት እንደሚልኩ መወሰን በእርስዎ ማህበረሰብ ውስጥ የትኞቹ አገልግሎቶች እንደሚገኙ እና ለቤተሰብዎ እና ለልጅዎ ምን በተሻለ ሁኔታ ይሰራል በሚለው ላይ የተመሠረተ ነው

  • ስለ ምዝገባ ሂደት እና የጊዜ ሰሌዳ የአካባቢዎን የመዋዕለ ሕፃናት አገልግሎት ያነጋገሩ እና ማዕከላቸውን እና ሰራተኞቻቸውን ይጎብኙ። የአከባቢዎን የመዋዕለ-ህፃናት ለማግኘት እና ለቤተሰብዎ ትክክለኛውን አገልግሎት እንዴት እንደሚመርጡ መረጃ:- How to choose a kindergarten ን ይጎብኙ

    ጥራት ያለው የመዋዕለ ህፃናት አገልግሎት መምረጥ አንድ ልጅ በመዋዕለ ሕፃናት ከሚያሳልፈው ጊዜ በጣም የሚጠቀምበትን ሁኔታ ያረጋግጣል። www.startingblocks.gov.auExternal Link ን በመጎብኘት የአገልግሎት ጥራት ደረጃዎችን ማየት ይችላሉ

  • በጥር እና ሚያዝያ መካከል የተወለዱ ልጆች ያላቸው ቤተሰቦች እና ተንከባካቢዎች ሁለንተናዊ የገንዘብ ወጪው የተሸፈነለት የሦስት ዓመት ልጆች መዋዕለ-ህፃናት የሚጀመርበትን ዓመት መምረጥ ይችላሉ፡ ፡ቤተሰቦች ከትምህርት መነሻ ዕድሜ ጋር ለማጣጣም በሚቀጥለው ዓመት ልጆቻቸው እንዲማሩ መምረጥ ይችላሉ፣ ሌሎች ልጆች ደግሞ ሲጀምሩም የሁለት ዓመት እድሜ ይሆናሉ፡፡

    በጥር 1 እና ሚያዚያ 30 መካከል የተወለዱ ልጆች፣ ሦስት ዓመት በሚሆኑበት ዓመተ-ምህረትም ይሁን አራት ዓመት በሚሆኑበት ዓመተ-ምህረት የሦስት ዓመት ልጆችን መዋዕለ-ህፃናት ለመሳተፍ ብቁ ናቸው፡፡

    ሁለት ዓመት ለሆኑ ሕፃናት አገልግሎቱ አስተማሪውን እና የልጆችን ንጥጥር ማሟላት በማይችልባቸው መርሃግብሮች ውስጥ ልጆች ሦስት ዓመት እስኪሞላቸው ድረስ ላይሳተፉ ይችላሉ፡፡

    በግንቦት 1 እና ታህሳስ 31 መካከል የተወለዱ ልጆች፣ አራት ዓመት በሚሆኑበት ዓመተ-ምህረት የሦስት ዓመት ልጆችን መዋዕለ-ህፃናት እና አምስት ዓመት በሚሆኑበት ዓመተ-ምህረት የአራት ዓመት ልጆችን መዋዕለ-ሕጻናት ለመሳተፍ ብቁ ናቸው፡፡

  • ልጅ የተወለደበት ቀን አስተያየቶች 2020 2021 2022 2023 2024

    ታህሳስ 21 2016 - ሚያዚያ 30 2017

    ቤተሰቦች በ2022 ወይም በ2023 ትምህርት የመጀመር ምርጫ አላቸው

    የ 3-አመት ልጆች መዋዕለ-ህፃናት

    የ 4-አመት ልጆች መዋዕለ-ህፃናት

    ቅድመ ዝግጅት ደረጃ 1 ደረጃ 2

    የ 3-አመት ልጆች መዋዕለ-ህፃናት

    የ 4-አመት ልጆች መዋዕለ-ህፃናት

    ቅድመ ዝግጅት ደረጃ 1
    ግንቦት 1 - ታህሳስ 20 2017 *

    የ 3-አመት ልጆች መዋዕለ-ህፃናት

    የ 4-አመት ልጆች መዋዕለ-ህፃናት

    ቅድመ ዝግጅት ደረጃ 1
    ታህሳስ 21 2017 - ሚያዚያ 30 2018

    ቤተሰቦች በ2023 ወይም በ2024 ትምህርት የመጀመር ምርጫ አላቸው

    የ 3-አመት ልጆች መዋዕለ-ህፃናት

    የ 4-አመት ልጆች መዋዕለ-ህፃናት

    ቅድመ ዝግጅት ደረጃ 1

    የ 3-አመት ልጆች መዋዕለ-ህፃናት

    የ 4-አመት ልጆች መዋዕለ-ህፃናት

    ቅድመ ዝግጅት

    ግንቦት 1 - ታህሳስ 20 2018*

    የ 3-አመት ልጆች መዋዕለ-ህፃናት

    የ 4-አመት ልጆች መዋዕለ-ህፃናት

    ቅድመ ዝግጅት

    *በመንግስት ትምህርት ቤቶች፣ ታህሳስ የመጨረሻው የመንፈቅ 4 ትምህርት ክፍለጊዜ ነው ።

    የቤተሰብ ምርጫ የሆነው ትምህርት ቤት ቀደም ያለ የመንፈቅ 4 ትምህርት ክፍለጊዜ፣ የመጨረሻ ቀን ካለው፣ ያ ቀን ጥቅም ላይ መዋል አለበት፡፡

    በጥር እና ሚያዝያ መካከል የተወለዱ ልጆች ያላቸው ቤተሰቦች እና ተንከባካቢዎች ሁለንተናዊ የገንዘብ ወጪው የተሸፈነለት የሦስት ዓመት ልጆች መዋዕለ-ህፃናት የሚጀመርበትን ዓመት መምረጥ ይችላሉ፡ ፡ቤተሰቦች ከትምህርት መነሻ ዕድሜ ጋር ለማጣጣም በሚቀጥለው ዓመት ልጆቻቸው እንዲማሩ መምረጥ ይችላሉ፣ ሌሎች ልጆች ደግሞ ሲጀምሩም የሁለት ዓመት እድሜ ይሆናሉ፡፡

    በጥር 1 እና ሚያዚያ 30 መካከል የተወለዱ ልጆች፣ ሦስት ዓመት በሚሆኑበት ዓመተ-ምህረትም ይሁን አራት ዓመት በሚሆኑበት ዓመተ-ምህረት የሦስት ዓመት ልጆችን መዋዕለ-ህፃናት ለመሳተፍ ብቁ ናቸው፡፡

    ሁለት ዓመት ለሆኑ ሕፃናት አገልግሎቱ አስተማሪውን እና የልጆችን ንጥጥር ማሟላት በማይችልባቸው መርሃግብሮች ውስጥ ልጆች ሦስት ዓመት እስኪሞላቸው ድረስ ላይሳተፉ ይችላሉ፡፡

    በግንቦት 1 እና ታህሳስ 31 መካከል የተወለዱ ልጆች፣ አራት ዓመት በሚሆኑበት ዓመተ-ምህረት የሦስት ዓመት ልጆችን መዋዕለ-ህፃናት እና አምስት ዓመት በሚሆኑበት ዓመተ-ምህረት የአራት ዓመት ልጆችን መዋዕለ-ሕጻናት ለመሳተፍ ብቁ ናቸው፡፡

    • የአከባቢዎ የመዋዕለ ህፃናት አገልግሎት ወይም አገልግሎት ሰጪ፣
    • የረጅም ወይም ሙሉ ቀን እንክብካቤ አገልግሎትን ሰጪን ጨምሮ የአከባቢዎ ምክር ቤት ወይም የእናቶች እና ልጆች ጤና ነርስ
    • ወደ የጤና መምሪያ (Department of Health - DH) የወላጅ መስመር በ 13 22 89 ይደውሉ
    • ወደ 3yo.kindergarten@education.vic.gov.au ኢሜልያድርጉ

    Three-Year-Old Kindergarten ን ይጎብኙ

Reviewed 07 February 2022